አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።
1 ሳሙኤል 23:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እርሱን በምትፈልግበት ጊዜ ወደ እኛ ና፤ እኛም እርሱን ለአንተ ለንጉሡ አሳልፈን ለመስጠት ኀላፊነትን እንወስዳለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ና እንጂ፣ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ደስ ባለህ ጊዜ ናና፥ እርሱን ለንጉሡ አሳልፎ መስጠት የእኛ ድርሻ ነው” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመውረድ ፈቃድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በንጉሡ እጅ ጥሎታልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ ንጉሥ ሆይ፥ ትወርድ ዘንድ ነፍስህ እንደ ወደደች ውረድ፥ በንጉሡም እጅ እርሱን አሳልፎ ለመስጠት እኛ አለን አሉት። |
አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።
ዳዊትም “የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎችስ ተከታዮቼንና እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡን ይሆን?” ሲል እንደገና ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል” ሲል መለሰ።