የቤተሰብ አባላት በአባታቸው ቤት አንዱን ወንድማቸውን መርጠው “አንተ ሌላው ቢቀር እንኳ የምትለብሰው ልብስ አለህ፤ ስለዚህ እባክህ አለቃችን ሁን፤ ፍርስራሽ ሁሉ በአንተ ሥልጣን ሥር ይሁን” ይሉታል።
1 ሳሙኤል 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ አሁን ምን ምግብ ትሰጠኛለህ? አምስት እንጀራ ወይም ያለህን ሌላ ነገር ስጠኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ አሁን በእጅህ ምን አለ? ዐምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ አሁን በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አምስት እንጀራ በእጅህ ካለ፥ ወይም በእጅህ ያለውን ስጠኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንስ በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ስጠኝ አለው። |
የቤተሰብ አባላት በአባታቸው ቤት አንዱን ወንድማቸውን መርጠው “አንተ ሌላው ቢቀር እንኳ የምትለብሰው ልብስ አለህ፤ ስለዚህ እባክህ አለቃችን ሁን፤ ፍርስራሽ ሁሉ በአንተ ሥልጣን ሥር ይሁን” ይሉታል።
ይህን ሕዝብ የምመራው እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤሜሌክን ወዲያ አስወግደው ነበር፤ ደግሞም ‘ሠራዊትህን በማጠንከር ወጥተህ ተዋጋ!’ ብዬ እነግረው ነበር።”
ዳዊትም ለካህኑ ለአቢሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እዚህ የመጣሁት የንጉሥ ሳኦልን ተልእኮ ለመፈጸም ነው፤ እኔ ወደዚህ የተላክሁበትን ጉዳይ ለማንም ሰው እንዳልገልጥ ንጉሡ አዞኛል፤ ተከታዮቼንም በአንድ ቦታ እንድንገናኝ አዝዣቸዋለሁ፤
ካህኑም “ከተቀደሰው ኅብስት በቀር ሕዝብ የሚመገበው እንጀራ የለኝም፤ ተከታዮችህ በቅርቡ ከሴቶች ጋር ሳይገናኙ ተቈጥበው በንጽሕና የቈዩ ከሆኑ፥ ይህን ኅብስት መብላት ይችላሉ” ሲል መለሰለት።