1 ሳሙኤል 20:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእሴይ ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተና መንግሥትህ ጸንታችሁ ለመኖር እንደማትችሉ አታውቅምን? አሁን ሄደህ አምጣው! እርሱ በሞት መቀጣት አለበት!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንህ መንግሥትህ አትጸኑም። መሞት ስለሚገባው፣ ሰው ላክና አስመጣልኝ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንህ መንግሥትህ አትጸኑም። መሞት ስለሚገባው፥ ሰው ላክና አስመጣልኝ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ መንግሥትህ አትጸናም፤ አሁንም ሞት የሚገባው ነውና ያን ብላቴና ያመጡት ዘንድ ላክ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእሴይም ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ አንተና መንግሥትህ አትጸኑም፥ አሁንም የሞት ልጅ ነውና ልከህ አስመጣልኝ አለው። |
ንጉሥ ሆይ! የአባቴ ቤተሰብ ሁሉ በሞት መቀጣት የሚገባው ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን በገበታህ ቀርቤ እንድመገብ መብት ሰጠኸኝ፤ ከዚህ የበለጠም ቸርነት እንዲደረግልኝ መጠየቅ አይገባኝም።”
የሳኦልም ቊጣ በዮናታን ላይ ነድዶ እንዲህ አለ፤ “አንተ የጠማማና የዐመፀኛ ሴት ልጅ! በራስህ ላይ ኀፍረትንና በእናትህም ላይ ውርደትን ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወዳጀትህን ደኅና አድርጌ ዐውቃለሁ!
በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለ ተማመንን የሰጠኸኝን የተቀደሰ ተስፋ በመጠበቅ እባክህ ለእኔ ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርግልኝ፤ ወንጀለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ እንጂ እንዲገድለኝ ወደ አባትህ ለምን ትወስደኛለህ?”
“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”
ይህ የሠራኸው ሥራ ልክ አይደለም፤ አበኔር፥ እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፥ እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን ጌታችሁን ንጉሡን መጠበቅ ስላልቻላችሁ ሁላችሁም ሞት ይገባችኋል! በራስጌው የነበረው የንጉሡ ጦርና እንዲሁም የውሃ መቅጃው አሁን የት እንዳለ እስቲ ተመልከት!” አለው።