እግዚአብሔርን የማያውቁ ሁሉ፥ በእውነት በባሕርያቸው ከንቱ ናቸው፤ ከሚታዩት መልካም ነገሮች፥ እርሱ የሆነውን ወደ ማወቅ አልደረሱም፤ አልያም የእጁን ሥራዎች በመመልከት፥ ሠሪውን ማስተዋል አልቻሉም።
እግዚአብሔርን የማወቅ ጕድለት በልቡናቸው ያለባቸው ሰዎች ሁሉ በእውነት ከንቱ ናቸውና፥ በሚታዩ መልካም ነገሮች ያለውን ያውቁ ዘንድ ተሳናቸው፥ ሥራውንም እያዩ ሠሪውን አላወቁትም።