ራእይ 21:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርም ክብር ነበረባት፥ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ፥ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በእግዚአብሔር ክብር ታበራ ነበር፤ የብርሃኗም ድምቀት እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ፣ እንደ መስተዋት የጠራ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ክብር ታበራ ነበር፤ የብርሃንዋም ድምቀት እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ፥ እንደ ብርሌ የጠራ የእያሰጲድ ዕንቊ ነበረ፤ |
ከዚያም ጌታ በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፤ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤
ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ።
በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሔር ክብርና ከኀይሉ የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ መቅደሱ መግባት አልቻለም።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።