እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
ደነዝና አላዋቂ ሆንሁ፤ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥ ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ።
አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀሌንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜ የተገዳደሩህን ዐስብ።
ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን? ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ቀለልን?
ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ
በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው! ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
የማያስተውል ሰው አያውቅም። አላዋቂ አይረዳውም።
እኔ በእውነት ከሰው ሁሉ ይልቅ ደንቆሮ ነኝ፥ የሰውም ማስተዋል የለብኝም።
እኔ በልቤ ስለ ሰው ልጆች፦ እንደ እንስሳ መሆናቸውን እንዲያዩ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል አልሁ።
በሬ ጌታውን፤ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።”