ነጋድራሶችና ነጋዴዎች የሚያመጡትን ወርቅ የሚጨምር አልነበረም፤ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምንት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር።
መዝሙር 68:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸንበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣ በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኰርማ መንጋ ገሥጽ፤ ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ ጦርነትን የሚወድዱ ሕዝቦችንም በትናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥ በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። |
ነጋድራሶችና ነጋዴዎች የሚያመጡትን ወርቅ የሚጨምር አልነበረም፤ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምንት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር።
እያንዳንዱም ገጸ በረከቱን፥ የወርቅንና የብርን ዕቃ፥ ልብስንና የጦር መሣሪያን፥ ሽቶውንም፥ ፈረሶችንና በቅሎችን እየያዘ በየዓመቱ ያመጣ ነበር።
ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥
እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።