“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!
መዝሙር 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማደሪያው ቦታ ሆኖ በምድር ወደሚኖሩ ሁሉ ተመለከተ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣ በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙፋኑ ላይ ሆኖ በምድር ላይ ያሉትን ሁሉ ያያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን ሻት፥ ተከተላትም። |
“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!
በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በደላቸውን ይቅር በል፤ እርዳቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው።
አንተ ጸሎቱን ስማ፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ የዚህን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ።
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ለእርሱ ክብርና የዘለዓለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።