መዝሙር 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣ በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ ንጉሤን ሾምኩ” ይላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በእነርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ በተቀደሰ ተራራው በጽዮን ላይ። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ራሴ ከረጅሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን ወስጄ አስቀምጠዋለሁ፥ ከጫፎቹ አንዱን ቀንበጥ እቀነጥበዋለሁ፥ በረጅምና ከፍ ያለ ተራራም ላይ እተክለዋለሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሠራዊት ጌታም ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።
ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
ከዚያም አየሁ፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።