በሰነፍ ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ።
በሰነፍ ሰው ዕርሻ በኩል ዐለፍሁ፤ በልበ ቢስ ሰው የወይን ቦታ ዐልፌ ሄድሁ፤
በሰነፍና ማስተዋል በጐደለው ሰው እርሻ ውስጥ በወይኑም አትክልት ቦታ ሄድኩኝ፤
እግዚአብሔር ጥበብን አስተማረኝ፥ የቅዱሳንንም ዕውቀት ዐወቅሁ።
“ስማኝ ልንገርህ፥ እነሆም ያየሁትን ልተርክልህ፤
እኔ እንዳየሁት፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ መከራንም የሚዘሩ ይህንኑ ያጭዳሉ።
እነሆ፥ ይህችን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፥ አንተም ለራስህ እወቀው።”
ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፥ ክፋት በሙሉ አፉን ይዘጋል።
ጐለመስሁ አረጀሁም፥ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።
በብልሃተኛ ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፥ በትር ግን አእምሮ ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።
መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮ የጐደለው ነው፥ እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።
ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ክፉም በክፋቱ ረጅም ዘመን ሲኖር፥ ይህን ሁሉ ከንቱ በሆነ ዘመኔ አየሁ።