መንገዱን ተምረህ፥ ለነፍስህም ወጥመድ እንዳታገኝህ።
አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ ራስህም ትጠመድበታለህ።
የእርሱን ጠባይ ከተማርክ አትላቀቅም።
መንገዱን እንዳትማር፥ ለነፍስህም ወጥመድ እንዳያገኝህ።
ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።
በክፉዎች መንገድ አትግባ፥ በመጥፎ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ።
አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”
የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።