ዘኍል 33:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማራም ተጉዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማራ ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጥተው በዚያ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደሚገኙባት ወደ ኤሊም ሄደው በዚያ ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምረትም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች፥ ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም በውኃ አጠገብ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። |