ዘኍል 31:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አላቸው፦ “በውኑ ሴቶችን ሁሉ በሕይወት እንዲኖሩ ፈቀዳችሁላቸውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ሴቶችን ሁሉ እንዴት በሕይወት ትተዉአቸዋላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ሲል ጠየቃቸው፦ “ሴቶችን በሙሉ በሕይወት ያስቀራችሁት ለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አላቸው፥ “ሴቶችን ሁሉ ለምን አዳናችኋቸው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አላቸው፦ በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን? |
ሽማግሌ፥ ወጣት፥ ድንግል፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ግደሉ፥ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፥ በመቅደሴም ጀምሩ። በቤቱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፥ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ አምላክህ ጌታ ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም የተዳፋቱንም ስፍራ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘውም እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ”