ነህምያ 7:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮ የተመለሱት የቤተ መቅደስ ሠራተኞችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ብዛት ጠቅላላ ድምር 392 ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። |
ከቴልሜላሕ፥ ከቴል ሀርሻ፥ ከክሩብ፥ ከአዶንና ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤትና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤