ሚክያስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቤን ሥጋ በሉ፥ ቁርበታቸውን ከላያቸው ላይ ገፈፉ፥ አጥንታቸውን ሰበሩ፤ በአፍላል እንዳለ በድስትም ውስጥ እንደሚከተት ሥጋ ቆራርጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቤን ቆዳ ገፋችሁ አጥንታቸውን ቈራርጣችሁ ለአፍላልና ለድስት እንደሚቈራረጥ ሥጋ አደረጋችኋቸው፤ ሥጋቸውንም በላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው። |
ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ በሰላም ሳይፈሩ የሚያልፉትን ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፥ ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።