ዘሌዋውያን 25:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽኑ እጅ አትግዛው፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጭካኔ አትግዛቸው፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን በማስጨነቅ አትግዛቸው፤ ነገር ግን እኔን አምላክህን ፍራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሥራ አታስጨንቀው፤ ነገር ግን አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጽኑ እጅ አትግዛው፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። |
አሁንም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ልጆች ባርያዎች ሆነው እንዲገዙላችሁ ታስባላችሁ፤ ነገር ግን አምላካችሁን ጌታን የበደላችሁት በደል በእናንተ ዘንድ የለምን?
ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።
የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “የተወሰነላችሁን የጡብ ሥራ ትናንትናና ዛሬ ለምን እንደ ቀድሞው አልጨረሳችሁም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።
“ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
የደከሙትን አላበረታችሁም፥ የታመመውን አላከማችሁትም፥ የተሰበረውን አልጠገናችሁትም፥ የባዘነውን አልመለሳችሁትም፥ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆና ገዛችኋቸው።
ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
እናንተም ጌቶች ሆይ! ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ታውቃላችሁ።