ዘሌዋውያን 25:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)46 ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም46 እነርሱንም እንደ ንብረት ለልጆቻችሁ አውርሷቸው፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ባሪያዎች ይሁኗችሁ፤ እስራኤላውያን ወገኖቻችሁን ግን በጭካኔ አትግዟቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም46 እነርሱንም በውርስ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አገልጋዮቻችሁ ይሆናሉ፤ ከእስራኤላውያን ወገኖቻችሁ መካከል ግን ማንንም በማስጨነቅ አትግዙ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)46 ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ታወርሱአቸዋላችሁ፤ እነርሱም ለእናንተ ለዘለዓለም ውርስ ይሆናሉ፤ ነገር ግን ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ማናቸውም ሰው ወንድሙን በሥራ አያስጨንቀው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)46 ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ይወርሱአቸው ዘንድ ተዉአቸው፤ ከእነርሱም ባሪያዎችን ለዘላለም ትወስዳላችሁ፤ ነገር ግን የእስራኤልን ልጆች ወንድሞቻችሁን በጽኑ እጅ አትግዙአቸው። Ver Capítulo |