2 ዜና መዋዕል 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አሁንም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ልጆች ባርያዎች ሆነው እንዲገዙላችሁ ታስባላችሁ፤ ነገር ግን አምላካችሁን ጌታን የበደላችሁት በደል በእናንተ ዘንድ የለምን? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች፣ ባሪያዎቻችሁ ልታደርጓቸው ትፈልጋላችሁ፤ እናንተስ ብትሆኑ ኀጢአት ሠርታችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አልበደላችሁምን? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ይህም አልበቃ ብሎአችሁ የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ወንዶችና ሴቶች በሙሉ የእናንተ ባሪያዎች ልታደርጉአቸው ታስባላችሁ፤ እናንተስ ይህን ስታደርጉ ኃጢአት በመሥራት አምላካችሁን እግዚአብሔርን ማሳዘናችሁ አይደለምን? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ልጆች ባሪያዎች አድርገን እንግዛ ትላላችሁ፤ የፈጣሪያችሁ የእግዚአብሔር ምስክር የምሆን እኔም ከእናንተ ጋር ያለሁ አይደለምን? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አሁንም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ልጆች ባሪያዎች ሆነው ይገዙላችሁ ዘንድ ታስባላችሁ፤ ነገር ግን አምላካችሁን እግዚአብሔርን የበደላችሁት በደል በእናንተ ዘንድ የለምን? Ver Capítulo |