ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።
ዘሌዋውያን 23:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀን ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባት ቀን መሥዋዕቱን በእሳት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ መሥዋዕትን በእሳት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የተለመደ ተግባራችሁንም አታከናውኑበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰባቱም ቀኖች በእያንዳንዱ ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አቅርቡ፤ ይህም ጉባኤውን የምትፈጽሙበት ቀን ስለ ሆነ ምንም ሥራ አትሥሩበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ስምንተኛዋም ቀን የተቀደሰች ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቡ፤ የመሰናበቻ በዓል ነውና፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባንን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን ቍርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት። |
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።