ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
ዘሌዋውያን 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና አመንዝራይቱን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም በባልዋ የተፈታችውን አያግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ናቸውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአምላኩ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና ጋለሞታን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም ከባልዋ የተፋታችውን አያግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና ጋለሞታን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም ከባልዋ የተፈታችውን አያግባ። |
ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።
መበለቲቱንና የተፈታችውን ለሚስትነት አይውሰዱ፤ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር የሆነችውን ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረችውን መበለት ይውሰዱ።