Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 21:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ካህኑ ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና አመንዝራይቱን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም በባልዋ የተፈታችውን አያግባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጋለ​ሞ​ታን ሴት ወይም የረ​ከ​ሰ​ች​ውን አያ​ግባ፤ ወይም ከባ​ልዋ የተ​ፋ​ታ​ች​ውን አያ​ግባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና ጋለሞታን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ፤ ወይም ከባልዋ የተፈታችውን አያግባ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 21:7
7 Referencias Cruzadas  

ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍች ወረቀት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።


መበለቶችን ወይም ፈት ሴቶችን አያግቡ፤ ነገር ግን ከእስራኤል ዘር የሆኑ ድንግሎችን ወይም የካህናት ሚስቶች የነበሩትን መበለቶች ማግባት ይችላሉ።


የአምላክህን ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።


እንዲሁ ሴቶችም የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos