ራሱንም ከከረጢቱ አውጥታ አሳየቻቸው፤ እንዲህም አለች፦ “የአሦር ሠራዊት ዋና የጦር አዛዥ የሆሎፎርኒስ ራስ ይኸውላሁ፤ ሰክሮ በተኛበት ቦታ የተጋረደው መጋረጃም ይኸውላችሁ፤ ጌታ በሴት እጅ መታው።
ቸብቸቦውንም ከከረጢቷ አውጥታ አሳየቻቸው፤ “የአሦር ሠራዊት አለቃ የሆሎፎርኒስ ቸብቸቦ እነሆ፥ በሚጠጣ ጊዜ ተንተርሶት የሚተኛበት ሰይፉም እነሆ፥ እግዚአብሔር በእኔ በሴቷ አድሮ ገደለው።