ከዚያም ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።
መሳፍንት 20:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በጌታ ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን?” ብለው ጌታን ጠየቁ። ጌታም፥ “አዎን፤ ውጡና ውጉቸው” ብሎ መለሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመግጠም እንደ ገና እንውጣን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ውጡና ግጠሟቸው” ብሎ መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንዝመትን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፦ “አዎ፥ በእነርሱ ላይ ዝመቱ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፥ እግዚአብሔርንም፦ ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን? ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም፦ በእነርሱ ላይ ውጡ አለ። |
ከዚያም ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በጌታ ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ልትሰጠን ልታጠፋንም ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? በዮርዳኖስ ማዶ መቀመጥን በወደድን ነበር እኮ!
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
“አንተም ጉዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው ባሉጥ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፥ ሌላው ሦስት ዳቦ፥ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል።
እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።