ኢዮብ 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳንህ ሰላምን እንደሚያገኝም ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ፥ አንዳችም አይጐድልብህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳንህ በሚያስተማምን ሁኔታ እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትቃኛለህ፤ አንዳችም አይጐድልብህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንኳንህ ሰላም እንደሚሰፍን ታረጋግጣለህ፤ የበጎችህንም በረት ስትጐበኝ ሁሉን በደኅና ታገኛቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜ ቤትህ በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፤ ከንብረትህም አንዳች አይጐድልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ አንዳችም አይጐድልብህም። |
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤