ኢዮብ 37:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጕዳል፤ እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አስደናቂ በሆነ ድምፁ ነጐድጓድን ያሰማል፤ እኛ ልንረዳው የማንችል ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያሉ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅ አድርጎ ያንጐደጕዳል፤ ለእንስሳት በየጊዜው ምግባቸውን ያዘጋጃል፥ የሚተኙበትንም ጊዜ ያውቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይደንግጥብህ፤ ሥጋህም ልብህም ከግዘፉ አይለወጥብህ፤ እርሱም እኛ የማናውቀውን ታላቅ ነገር ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል። |
ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለማዊነትን በልቡ ሰጠው።
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።