ኢዮብ 24:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን ቀምተው ያሰማራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤ የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ክፉ ሰዎች ድንበር ያፈርሳሉ። በጎችንም እየሰረቁ ያሰማራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣን የድንበሩን ምልክት አለፉ፤ እረኛውንም ከመንጋዎቹ ጋር ይነጥቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፥ መንጋዎቹን በዝብዘው ያሰማራሉ። |
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።
“አምላክህ ጌታ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ።