ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዮብ 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኀጢአተኞች መፈንጨት ለዐጭር ጊዜ፣ የክፉዎችም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክፉ ሰው ድንፋታ ለአጭር ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔርንም የሚክዱ ሰዎች ደስታቸው በቅጽበት የሚጠፋ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀጢኣተኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝንጉዎችም ደስታ ጥፋት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑን የዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን? |
ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።