ኢዮብ 19:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆዳዬ ተበልቶ ቢያልቅም፥ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማየው ዐውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ቍርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያ ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ። |
አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።