Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያ ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያ ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን፤ አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እግዚአብሔር እኔን የሚያውቀኝን ያኽል ሙሉ ዕውቀት ይኖረኛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁን ግን ታወ​ቀኝ፤ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ፤ በመ​ስ​ታ​ወ​ትም እን​ደ​ሚ​ያይ ሰው ዛሬ በድ​ን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ እና​ያ​ለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እና​ያ​ለን፤ አሁን በከ​ፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ መጠን ሁሉን አው​ቃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 13:12
20 Referencias Cruzadas  

ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።


እኔ ግን አሁን ይህን አላገኘሁትም ወይም አሁን ፍጹም ለመሆን አልበቃሁም፤ ዳሩ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ አድርጎኛልና ይህን የራሴ ለማድረግ ወደ ፊት እሮጣለሁ።


ፊቱንም ያያሉ፤ ስሙም በግምባሮቻቸው ይኖራል።


ቃሉን የሚሰማና የማያደርግ ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤


የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።


ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።


ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ የታወቀ ነው።


የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።


እኔ በምሳሌ ሳይሆን እፊት ለፊት ከእርሱ ጋር በግልጥ እነጋገራለሁ፤ የጌታንም ሀልዎተ-ቅርፅ ይመለከታል፤ ታዲያ፥ በባርያዬ በሙሴ ላይ ለመናገር ለምን አልፈራችሁም?”


ስለዚህ ያዕቆብ፦ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሆኖም ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ጵኒኤል” ብሎ ጠራው።


“ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


አብም እንደሚያውቀኝ፥ እኔም አብን እንደማውቀው፤ ነፍሴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ።


ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ጌታም ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር። ሙሴ ወደ ሰፈሩ ሲመለስ አገልጋዩ የሆነው ወጣቱ የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እንቆቅልሽ ጠይቅ፥ ለእስራኤልም ቤት ምሳሌን መስል፥


ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ።


እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።


ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላስል ነበር። ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios