ኢዮብ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣ ወርሶሃል፥ ስለ አንተ ሲባል፥ ምድር ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ በቍጣ የነደድህ እንደ ሆነ፣ ምድር ባዶዋን ትቀራለች? ወይስ ዐለት ከስፍራው ይወገዳል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ብትቈጣ ራስህን ትጐዳለህ እንጂ በአንተ ቊጣ ምድር ባዶ አትሆንም። አለቶችም ከስፍራቸው አይነቃነቁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው? ከሰማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ተራራዎች ከመሠረታቸው ይናወጣሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣ ወርሶሃል፥ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ፥ ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን? |
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።
በተነሣበት ጊዜ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፏጫል፤ ሰውነቱም ይደርቃል፤ ርኩስ መንፈሱን እንዲያስወጡት ደቀ መዛሙርትህን ጠየቅኋቸው፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”