ኢዮብ 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይረበሻሉ፥ ንጹሕም አምላኩን በሚክድ ላይ ይበሳጫል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኞች በዚህ ነገር ተደናግጠዋል፤ ንጹሖች እግዚአብሔርን በማያምኑ ሰዎች ላይ ተቈጥተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስታዬን ተማምኛት ነበር፤ ነገር ግን ጠፋችብኝ፤ አግባብስ ወደ ኃጥኣን ትመለስ ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሕም በዝንጉው ላይ ይበሳጫል። |
ዐይኖችህ ክፉ እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፥ ክፉ ሥራም መመልከት አትችልም፤ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉዎቹ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆኑትን ሲውጡ ለምን ዝም ትላለህ?
ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።