ኤርምያስ 49:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጐልማሶችዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ወታደሮችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤ በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን የዚያች ከተማ ወጣቶች በከተማይቱ መንገዶች ላይ ይገደላሉ፤ ወታደሮችዋም ይደመሰሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጐበዛዝቷ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፤ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይወድቃሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ሀብትሽ፥ ሸቀጥሽ፥ ንግድሽ፥ መርከበኞችሽ፥ መርከብ መሪዎችሽ፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ፥ ሸቀጥሽን የሚነግዱ፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ወታደሮችሽ ሁሉ፥ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በውድቀትሽ ቀን ወደ ባሕር ልብ ይወድቃሉ።
“በግብጽ እንደነበረው ቸነፈርን በመካከላችሁ ላክሁባችሁ፤ ጉልማሶቻችሁንም በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፤ የሰፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ አወጣሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።