ሕዝቅኤል 27:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ሀብትሽ፥ ሸቀጥሽ፥ ንግድሽ፥ መርከበኞችሽ፥ መርከብ መሪዎችሽ፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ፥ ሸቀጥሽን የሚነግዱ፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ወታደሮችሽ ሁሉ፥ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በውድቀትሽ ቀን ወደ ባሕር ልብ ይወድቃሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 የንግድ ሸቀጥ ሀብትሽ ሁሉ፥ መርከብ ነጂዎችሽ ሁሉ፥ በመርከብ ውስጥ የሚያገለግሉ ጠጋኞችሽና ነጋዴዎችሽ ሁሉ፥ በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩ ወታደሮች ሁሉ፥ መርከቦችሽ ሲሰባበሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ ባሕር ይሰጥማሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ኀይልሽና ዋጋሽ፥ ንግድሽም፥ መርከበኞችሽም፥ መርከብ መሪዎችሽም፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ ነጋዴዎችሽም፥ በአንቺም ዘንድ ያሉ ሰልፈኞችሽ ሁሉ በውስጥሽ ከአሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወደቅሽበት ቀን በባሕር ውስጥ ይጠፋሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ብልጥግናሽና ሸቀጥሽ ንግድሽም መርከበኞችሽም መርከብ መሪዎችሽም ሰባራሽንም የሚጠግኑ ነጋዴዎችሽም በአንቺም ዘንድ ያሉ ሰልፈኞችሽ ሁሉ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወደቅሽበት ቀን በባሕር ውስጥ ይወድቃሉ። Ver Capítulo |