ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
ኤርምያስ 48:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞአብ ምድር ጠፍተዋል፤ ወይን ከመጥመቂያው ጠፍቶአል፤ በነግህ የሚጠምቁት የለም፤ በሠርክም የሚያደርጉት የእልልታ ድምፅ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፥ ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ፥ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም። |
ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
በዚያን ጊዜ አንድ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት መጣ፥ የተገኘው ግን ዐሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፤ አምሳ ማድጋ ለመቅዳት ወደ ወይን መጥመቂያው መጣ፥ የተገኘው ግን ሀያ ብቻ ነው።