ኢሳይያስ 55:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእሾህም ፈንታ ጥድ፥ በኩርንችትም ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ ለጌታም መታሰቢያና ለዘለዓለምም የማይጠፋ ምልክት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣ በኵርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል። ይህም የእግዚአብሔር መታሰቢያ፣ ሊጠፋ የማይችል፣ የዘላለም ምልክት ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእሾኽ ፈንታ ዝግባ በኲርንችትም ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያና ለዘለዓለምም የማይጠፋ ምልክት ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእሾህም ፋንታ ጥድ፥ በኵርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ የእግዚአብሔርም ስም ለዘለዓለም በማይጠፋ ምልክት ይመሰገናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእሾህም ፈንታ ጥድ በኵርንችትም ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል፥ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያና ለዘላለምም የማይጠፋ ምልክት ይሆናል። |
ይህም ለሠራዊት ጌታ በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው ምክንያት ወደ ጌታ በመጮኻቸው፥ እርሱ መድኃኒትንና ኃያልን ሰዶ ያድናቸዋል።
እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፥ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤
ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።
ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የጌታ መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፤ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።
መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም፥ ምስጋናና ክብር እንዲሆኑልኝ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ነገር ግን አልሰሙም።”
የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።
ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።
ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ካሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቆስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።
እነሆ፥ አንድ ሰው በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ በስተ ኋላውም ቀይና ነጭ አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።
ከሥጋችሁ ደካማነት የተነሣ እንደ ሰው አነጋገር እናገራለሁ። የሰውነታችሁን ክፍሎች ሕገ ወጥነትን ለሚያመጣ ለርኩሰትና ለሕገ ወጥነት ባርያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ ስለዚህ አሁን የሰውነታችሁን ክፍሎች ቅድስና ለሚያመጣ ለጽድቅ ባርያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።