ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።
ኢሳይያስ 37:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም ላይ በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት’ ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬም ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሀገሩ ስላለ ጉዳይ በሹክሹክታ ወሬ እንዲሸበርና ወደ ሀገሩ ተመልሶ በሰይፍ እንዲገደል አደርገዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ መንፈስን በላዩ እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፥ ወሬንም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፥ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት አላቸው። |
ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።
ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
የአሦርም ንጉሥ፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቷል” የሚል ወሬ ሰማ። ይህን በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህም አለው፦