ምድርም ሁሉ አርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች እልልም ብላለች።
ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤ የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።
በመጨረሻ ግን እነሆ ዓለም ሁሉ የሰላም ዕረፍት ያገኛል፤ ሁሉም በደስታ ይዘምራሉ።
ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች፤ እልልም ብላለች።
ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
የዳዊት መዝሙር። ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፥ ቀኙ፥ የተቀደሰ ክንዱም ለእርሱ ማዳን አደረገ።
በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል፥ በክፉዎችም ጥፋት እልል ትላለች።
አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ።
ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፥ ዘምሩ፥ ምድር ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፥ እልል በሉ።
አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ በባቢሎን ላይ እልል ይላሉ፥ ይላል ጌታ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ስትደሰት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ።
እነርሱም በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ ለነበረው ለጌታ መልአክ፥ “ምድርን አሰስናት፥ እነሆም፥ መላዋ ምድር በጸጥታ ዐርፋ ተቀምጣለች” ብለው መለሱለት።
“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”