ዕብራውያን 10:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ገና “በጣም ጥቂት ጊዜ፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል፥ አይዘገይምም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም “ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ያ የሚመጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ አይዘገይምም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚመጣውም ፈጥኖ ይደርሳል፥ አይዘገይምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤ |
አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።