ዘፍጥረት 49:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደ ፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፥ “በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኍለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብስቡ። |
በዘመኑም ፍጻሜ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።
ይህም ነገር የሠራዊት ጌታ ይህንን በጆሮዬ ነገረኝ፤ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል ጌታ።
እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? ጌታ የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።
እንዲህም ይሆናል፥ በመጨረሻው ዘመን የጌታ ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶች በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
“እግዚአብሔር ይላል ‘በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤
ይሰሙና ጌታ አምላካችሁንም መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና በከተሞችህ የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስብ።
መንፈስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ፤
ከዚያ በኋላም አየሁ፤ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ! እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበትን ነገር አሳይሃለሁ፤” አለ።