እንዲህም አለ፦ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እለምንሃለሁ፥ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፥ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ።
ዘፍጥረት 27:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ልጁን፦ “ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው?” አለው። እርሱም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ልጁን፣ “ልጄ ሆይ፤ ከመቼው ቀንቶህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “እግዚአብሔር አምላክህ አሳካልኝ” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅም “ልጄ ሆይ፥ እንዴት በቶሎ ልታገኝ ቻልክ?” አለው። ያዕቆብም “አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልኩ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥነህ ያገኘኸው ይህ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፥ “አምላክህ እግዚአብሔር በፊቴ የሰጠኝ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ። |
እንዲህም አለ፦ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እለምንሃለሁ፥ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፥ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ።