ዘፍጥረት 25:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።) አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳውም ያዕቆብን፣ “ቶሎ በል፤ በጣም ርቦኛልና ከዚህ ቀይ ወጥ አብላኝ” አለው። ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ያዕቆብን “ከዚህ ከቀይ ወጥ ስጠኝ” አለው። ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከምስር ንፍሮህ አብላኝ፤ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና” አለው፤ ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ። |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት
የአብድዩ ራእይ። ጌታ አምላክ ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከጌታ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በጦርነት እንነሣ ብሏል።