ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”
ዘፍጥረት 24:65 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሌውንም፦ “ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው?” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩንም፣ “ይህ ሊገናኘን በመስኩ ውስጥ ወደዚህ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል ጠየቀችው። አገልጋዩም፣ “ጌታዬ ነው” ብሎ መለሰላት፤ እርሷም መሸፈኛዋን ተከናነበች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት። ስለዚህ በፍጥነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውንም፥ “ሊቀበለን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማነው?” አለችው። ሎሌውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እርስዋም ቀጸላዋን ወስዳ ተከናነበች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። |
ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”
የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን።