ዘፍጥረት 1:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “በምድር ላይ ያሉትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ፣ በፍሬአቸው ውስጥ ዘር ያለባቸውን ዛፎች ሁሉ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ ሰጥቻችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ምግብ እንዲሆኑአችሁ በምድር ገጽ ላይ የሚገኙትን የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን ሁሉ ሰጥቻችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለዉን ሐመለማል ሁሉ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራዉንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፤ |
ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”
ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ ‘እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና፤’ ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤ እንኖርማለን።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።