ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
ሕዝቅኤል 17:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሐላውን ስለ ናቀ፥ ቃል ኪዳኑንም ስላፈረሰ፥ እነሆም እጁን ሰጠ፥ እነዚህንም ሁሉ አደረገ፥ ስለዚህ አያመልጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያደረገውን መሐላ በማቃለልና እጁን ያስገባበትን ውል በማፍረስ ይህን ሁሉ ስለ ፈጸመ ከቅጣት አያመልጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ መሐላውን በመናቅ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሰና እጁን ከሰጠ በኋላ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስላደረገ አያመልጥም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል ኪዳኑንም በማፍረስ መሐላውን ንቆአል፤ እነሆም እጁን አሳልፌ ሰጠሁ፤ ይህንም ሁሉ አድርጎአል፤ ስለዚህም አያመልጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃል ኪዳኑንም በማፍረስ መሐላውን ንቆአል፥ እነሆም፥ እጅን ሰጠ፥ ይህንም ሁሉ አድርጎአል፥ ስለዚህ አያመልጥም። |
ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለጌታ ስጡ፥ ለዘለዓለም ወደተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቁጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን ጌታን አገልግሉ።
ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?
እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ መሐላውን የናቀበት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውን ቃል ኪዳኑን ያፈረሰበት፥ ያነገሠው ንጉሥ በሚኖርበት ስፍራ በባቢሎን መካከል በእርግጥ ይሞታል።