Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 30:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለጌታ ስጡ፥ ለዘለዓለም ወደተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቁጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን ጌታን አገልግሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደ አባቶቻችሁም ዐንገተ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ እርሱ ለዘላለም ወደ ቀደሰውም መቅደስ ኑ። አስፈሪ ቍጣው ከእናንተ እንዲመለስም፣ እግዚአብሔር አምላካችሁን አገልግሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለእግዚአብሔር ታዘዙ እንጂ እንደ እነርሱ ልበ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘለዓለም ወደ ቀደሰው በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ ኑ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ቊጣውን ከእናንተ እንዲመልስ እርሱን ብቻ አምልኩ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አሁ​ንም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ አን​ገ​ታ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ስጡ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ወደ ተቀ​ደ​ሰው ወደ መቅ​ደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም ከእ​ና​ንተ እን​ዲ​መ​ልስ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 30:8
30 Referencias Cruzadas  

አሁንም የቁጣው ጽናት ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ በልቤ አስቤአለሁ።


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው።


እንግዲህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ይቆማሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ውስጥ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።


ስለ እስራኤል ግን “ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ይላል።


አሁን ግን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ባርያዎች ሆናችኋል፥ ፍሬያችሁም ቅድስና ነው፤ መጨረሻውም የዘለዓለም ሕይወት ነው።


የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “ሂድ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


የቁጣውን ንዳድ በላያቸው ሰደደ፥ መቅሠፍትን መዓትንም መከራንም በክፉዎች መላእክት ሰደደ።


ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።


በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን መንጋ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፥ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።


እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ።


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።


ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።


ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “በጌታ ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነውና።”


አሁንም ስሙኝ፤ የጌታ ቁጣ በላያችሁ ነድዶአልና ከወንድሞቻችሁ የወሰዳችኋቸውን ምርኮኞች መልሱ።”


ሹማምንቶቹም ሁሉ፥ ኃያላኑም፥ ደግሞም የንጉሡ የዳዊት ልጆች ሁሉ ለንጉሡ ለሰሎሞን ታማኞች እንደ ሆኑ ቃል ገቡለት።


ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።


ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”


ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ።


ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፥ በስሙም ማል።


አለቆቻችንም ለጉባኤው ሁሉ ይቁሙ፥ ስለዚህም ነገር የአምላካችን የነደደው ቁጣ ከእኛ እንዲመለስ፥ እያንዳንዳቸው በከተሞቻችን ያሉ እንግዶቹን ሴቶች ያገቡት ሁሉ በተቀጠረው ጊዜ ይምጡ፥ ከእነርሱም ጋር የከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ይምጡ።”


የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።


‘ህዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤት በዚያ እንዲሠራልኝ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥሁም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ እንዲሆን ማንንም አልመረጥሁም፤


ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፥ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’


አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ እንዲኖር ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios