የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፥ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፥
ሕዝቅኤል 16:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅ እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሽ እኅትሽም ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ የምትቀመጥ ሰዶም ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላቂቱ እኅትሽ ከአንቺ በስተሰሜን ከሴት ልጆቿ ጋራ የምትኖረው ሰማርያ ናት፤ ታናሺቱ እኅትሽም ከአንቺ በስተ ደቡብ ከሴት ልጆቿ ጋራ የምትኖረው ሰዶም ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ታላቅ እኅትሽ ከመንደሮችዋ ጋር በስተ ሰሜን የምትገኘው ሰማርያ ናት፤ ታናሽ እኅትሽም ከመንደሮችዋ ጋር በስተ ደቡብ የምትገኘው ሰዶም ናት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፤ ታናሽቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሺቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት። |
የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፥ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፥
እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፥ ድርሻሽንም ቀንሻለሁ፥ ከክፉ መንገድሽ የተነሣ ለሚያፍሩ፥ ለጠላቶችሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
ሰማርያ የኃጢአትሽን ግማሽ አልሠራችም፤ አንቺ ግን ከእነርሱ ይልቅ ርኩሰትሽን አበዛሽ፥ በሥራሽም ርኩሰት ሁሉ እኅቶችሽን ጻድቃን አስመሰልሻቸው።
የአንቺ ታላቅና የአንቺ ታናሽ እኅቶችሽን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪያለሽም፥ ሴቶች ልጆች እንዲሆኑሽም ለአንቺ እሰጣቸዋለሁ፥ ከቃል ኪዳንሽ የተነሣ ግን አይደለም።
ስማቸውም፦ የታላቂቱ ኦሆላ የእኅትዋም ኦሆሊባ ነበረ። የእኔም ሆኑ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም፦ ኦሆላ ሰማርያ ናት፥ ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።
ይህ ሁሉ ስለ ያዕቆብ በደልና ስለ እስራኤል ቤት ኃጢአት ነው። የያዕቆብ በደል ምንድነው? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ የኮረብታው መስገጃ ምንድነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።