Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስማቸውም፦ የታላቂቱ ኦሆላ የእኅትዋም ኦሆሊባ ነበረ። የእኔም ሆኑ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም፦ ኦሆላ ሰማርያ ናት፥ ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የታላቂቱ ስም ኦሖላ፣ የእኅቷም ኦሖሊባ ነበር፤ ሁለቱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውም፣ ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባም ኢየሩሳሌም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከእነርሱም ታላቂቱ ኦሆላ ትባል ነበር፤ እርስዋም ሰማርያ ነች፤ ታናሽቱ ደግሞ ኦሆሊባ ትባል ነበር እርስዋም ኢየሩሳሌም ነች፤ እኔ ሁለቱንም አግብቼ ልጆች ወለዱልኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ስማ​ቸ​ውም የታ​ላ​ቂቱ ሐላ የታ​ናሽ እኅ​ቷም ሐሊባ ነበረ፤ እኔም አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለዱ። ስማ​ቸ​ውም ሐላ ሰማ​ርያ ናት፤ ሐሊባ ደግሞ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ ሰማርያ ናት፥ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 23:4
22 Referencias Cruzadas  

በአንቺ በኩል አለፍሁ፥ አየሁሽም፥ እነሆ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበር፥ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ላይ ዘረጋሁና ዕርቃንሽን ሸፈንሁ፥ ማልሁልሽም ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም የእኔ ሆንሽ።


ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ እንድትሆኑና ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።


እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና።


የሚረብሽ ሕዝብ በአንቺ ላይ ያመጡብሻል፥ በድንጋይም ይወግሩሻል፥ በሰይፋቸውም ይቆራርጡሻል።


ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ ለእነርሱ መብል እንዲሆኑ ሠዋሻቸው። አመንዝራነትሽ አንሶ ነውን?


እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።


እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባኤአቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረም የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር።


‘ስሜ ይጠራበታል’ ወዳልከው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ፤ አገልጋይህም በዚህ ስፍራ የምጸልየውን ጸሎት ስማ።


ጌታም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ “ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም አመነዘረች።


ታላቅ እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሽ እኅትሽም ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።


በግብጽ አመነዘሩ፤ በወጣትነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ ጡቶቻቸው ተዳሰሱ፥ በዚያም የድንግልናቸው የጡቶች ጫፍ ተዳበሱ።


ኦሖላም የእኔ ሆና ሳለ አመነዘረች፥ ጦረኞች ከሆኑት አሦራውያን ውሽሞችዋ ጋር በፍትወት ተከተለቻቸው።


ጌታ እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሆላና በኦሆሊባ ትፈርዳለህን? ርኩሰታቸውን ንገራቸው።


ሰው ወደ አመንዝራ እንደሚገባ ወደ እርሷ ገቡ፤ ስለዚህ አመንዝራ ወደ ሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ።


እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት።


እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም እርሷ አሳፋሪ ነገር አድርጋለች፤ ምክንያቱም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ፥ ብላለችና።


‘ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች’ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም፤ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios