Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:61 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 የአንቺ ታላቅና የአንቺ ታናሽ እኅቶችሽን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪያለሽም፥ ሴቶች ልጆች እንዲሆኑሽም ለአንቺ እሰጣቸዋለሁ፥ ከቃል ኪዳንሽ የተነሣ ግን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ከአንቺ ታላላቅ የሆኑትንና ታናናሽ የሆኑትን እኅቶችሽን ስትቀበዪ፣ አካሄድሽን ታስቢአለሽ፤ ታፍሪአለሽም። ሴት ልጆች እንዲሆኑሽም እነርሱን ለአንቺ እሰጣለሁ፤ ከአንቺ ጋራ በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት ግን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 ታላቅና ታናሽ እኅቶችሽን ወስጄ ለአንቺ እንደ ልጆችሽ አድርጌ በምሰጥበት ጊዜ የቀድሞውን አካሄድሽን አስታውሰሽ ታፍሪአለሽ። ይህ የሚሆነው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 ታላ​ቆ​ቹ​ንና ታና​ሾ​ቹን እኅ​ቶ​ች​ሽ​ንም በተ​ቀ​በ​ልሽ ጊዜ መን​ገ​ድ​ሽን ታስ​ቢ​ያ​ለሽ፤ ታፍ​ሪ​ማ​ለሽ፤ ለአ​ን​ቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ቃል ኪዳ​ንሽ ግን አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 እኅቶችሽንም ታላቂቱንና ታናሺቱን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪማለሽ፥ ለአንቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰጣቸዋለሁ፥ ስለ ቃል ኪዳንሽ ግን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:61
31 Referencias Cruzadas  

ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።


ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሟቸዋል።


ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በዚያም የረክሳችሁባትን መንገዳችሁንና ሥራችሁን ሁሉ ታስባላችሁ፤ ስለ ሠራችሁትም ክፋታችሁ ሁሉ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ የምሠራው ስለ እናንተ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው በመንግሥታት መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ በኃጢአታቸው እንዲያፍሩ ለእስራኤል ቤት ስለ ቤቱ ንገራቸው፥ ንድፉንም ይለኩ።


በክህነት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደተቀደሰው ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አይቀርቡም፤ ስድባቸውንና የሠሩትን ርኩሰታቸውን ይሸከማሉ።


ያመለጡት ተማርከው በሄዱባቸው በአሕዛብ መካከል ሆነው ያስታውሱኛል፤ ምክንያቱም ከእኔ በራቀው አመንዝራ ልባቸውና፥ ጣዖቶቻቸውን በተከተሉ በአመንዝራ ዐይኖቻቸው ተሰብሬአለሁና፥ በክፉ ስራቸውና በርኩሰታቸውም ሁሉ ራሳቸውን ይጸየፋሉ።


እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ።


ተመልሰው መዳን እስከማይችሉ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በጭራሽ! ነገር ግን እነርሱን ለማስቀናት፥ በእነርሱ በደል፥ መዳን ለአሕዛብ ሆነ።


በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።


ምክንያቱም ክህነቱ ሲለወጥ፥ ሕጉ ደግሞ ሊለወጥ ግድ ይላልና ነው።


“አዲስ” በሚል ጊዜ ፊተኛውን አሮጌ አድርጎታል፤ ስለዚህ ጊዜው ያለፈበትና አሮጌው ነገር ሁሉ የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos