ስለዚህም ያ ነቢይ “የጌታን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።
ሕዝቅኤል 14:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ አውሬ በምድሪቱ እንዲያልፍ ባደርግ፥ ልጅ አልባ ቢያደርጋት፥ በአውሬው ምክንያት ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የዱር አራዊትንም በአገሪቱ ላይ ሰድጄ፣ አገሪቱን ሕፃናት አልባ ቢያደርጓትና ከአራዊቱም የተነሣ ምድሪቱ ሰው እስከማያልፍባት ባድማ ብትሆን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያች አገር አውሬ ሰድጄ ሰው አልባ እስከሚሆንና ማንም በዚያ በኩል ማለፍ እስከማይችል ድረስ አገሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ሀገር ላይ ክፉ አውሬን ባመጣ፥ ፈጽሜም ባጠፋት በዚያም አውሬ ፊት የሚያልፍ ባይገኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉዎቹን አራዊት በምድር ባሳልፍ እነርሱም ልጆችዋን ቢያጠፉ ስለ አራዊትም ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥ |
ስለዚህም ያ ነቢይ “የጌታን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።
እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፤
ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ ዐራቱን ዓይነት ጥፋት ልኬባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
“ለተራሮች ልቅሶንና እንጉርጉሮን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው ባድማ ሆነዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥
ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆችሽን ያሳጡሻል፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ በኩል ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።
በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።