La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ መንኰራኵሮችም በአጠገባቸው ነበሩ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ መንኰራኵሮቹም በአጠገባቸው ነበሩ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው መብረር ጀመሩ፤ መንኰራኲሮቹም ከጐናቸው ነበሩ፤ የእስራኤል አምላክ አንጸባራቂ ክብር ከበላያቸው ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፥ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችም በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በላ​ያ​ቸው ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ መንኰራኵሮችም በአጠገባቸው ነበሩ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 11:22
6 Referencias Cruzadas  

በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንዳለ ቀስተ ደመና የሚመስል፥ በዙሪያው የከበበው ብርሃንም እንዲሁ ይመስል ነበር። ይህም የጌታ ክብር መልክ አምሳያ ነበር። ባየሁትም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ፥ የሚናገር ድምፅም ሰማሁ።


ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ እኔም እያየሁ ከምድር ተነሡ፥ ሲወጡም መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በጌታ ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ላይ ነበረ።


የጌታ ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መግቢያ ላይ ቆመ፥ ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በጌታ የክብር ብርሃን ተሞላ።


እነሆ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ነበር፥ ከክብሩ የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።


የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።